Library

የጎንደር መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ቤተመፅሀፍና ዶክመንቴሽን

የጎንደር መምህራን ትምህርት  ኮሌጅ ቤተ-መፅሀፍቶች በዋናነት ሁለት ያሉት ሲሆን  አገልግሎቱም በተደራጀ መልኩ በባለሙያ  የሚመራ ነው፡፡

የስራ ዘርፍ  ሃላፊ/ተጠሪ /፡-  ብርቱካን ስማቸው , email :- lib@gcte.edu.et

በስራ ዘርፉ ያሉ ክፍሎች

 • ካታሎግ እና ክላስፊኬሽን
 • ሰርኩሌሽን
 • ባይንዲግ እና ሌሎችም
 • የስራ ዘርፉ የሰው ሃይል በሁለቱም ቤተ-መፅሃፍት

የሰው ሃይል ብዛት

 ሴት             ወንድ

   7               1

የትምህርት ደረጃ

 • 1 ሴት ማስተር
 • 2 ሴት ዲፕሎማ
 • 4 ሴት ዲግሪ፣ 1 ወንድ ዲግሪ

የስራ ዘርፉ ዋና ዋና ተግባራት

 • መጽሃፍትና ላሎች የቤተ-መጽሃፍት ንብረቶች በአግባቡ መያዝ፣ በየአመቱ የንብረት ቆጠራ ማካሄድ፣
 • የመጽሃፍትን ደህንነት ለመጠበቅ ልዩልዩ የአሰራር ስርአት መዘርጋት፣
 • የቤተመጽሀፍት ክበብ በማቋቋም ክበቡ እገዛ እንዲደርግና አባላት ከክበቡ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ፣
 • የመጽሀፍትን እድሜ ለማራዘም የመጽሀፍት ጥገና/ድጎሳ ተደርጓል፣ ጋዜጦች መደጎስ፣
 • የንባብ ባህልን ለማዳበር የሚያግዙ ልዩልዩ ስልቶች ቀይሶ ተግባራዊ ማድረግ፣
 • የአንባብን/የተገልጋዮች መረጃ በዘመናዊ መልክ መያዝ፣ ለባለድርሻ አካላት በየጊዜው በተለያዩ መንገዶች መግለጽ፣ አዳዲስ ዕትሞችን ለተጠቃሚዋች ማሳወቅ፣
 • ተፈላጊ መጽሃፍት በወቅቱ እንዲቀርቡ ማድረግ፣ አዳዲስ መፅሃፍትን ካርድ ካታሎግ ማዘጋጀት፣ ለተጠቃሚዋች ተገቢውን መረጃ መስጠት፣
 • ልዩልዩ ጋዜጦችና መጽሄቶች በወቅቱ ለአንባብያን እንዲቀርቡ ማድረግ፣
 • የአንባብያንን የንባብ ጊዜ በሚገባ ማክበር፣

ያሉት ፋሲሊቲዋች

 • በሁለት ቤተመጽሃፍት 11,981 መፅሃፍቶች ክምችት መኖሩ፣

000-099 Computer science, information & general works -1,110

100-199 Philosophy & psychology ——————————499

200-299 Religion —————————————————–53

300 -399Social sciences ——————————————-2,016

400-499 Language ————————————————987

500 -599Science ————————————————–3,007

600 -699Technology ——————————————–310

700 -799Arts & recreation———————————–320

800-899 Literature ——————————————-2,944

900-999 History & geography—————————-735

  አጠቃላይ ድምር——————————11,981

 

የቤተመጽሃፍቱ የ2011ዓ.ም የሁኔታዎች ትንተና (SWOT)

 1. ጥንካሬ (Strength)
 • በቤተ-መፃህፍቱ ውስጥ ያለው በጥንካሬ የምንይዘው
 • ሀላፊዎች ለቤተ-መፃህፍቱ ልዩ ትኩረት በመስጠት ድጋፍ ማድረጋቸው፤
 • መጽሀፎችና መጽሄቶች ጋዜጦች በአግባቡ የተደራጁ መሆናቸው
 • ሰራተኞች ከሞላ ጎደል ስለ ቤተ-መፃህፍት አጠቃቀምና አሰራር ግንዛቤ ያላቸው መሆኑ ፤
 • ለመጽሀፍ ጥገና የሚያገለግሉ ማቴሪያሎች በወቅቱ እየቀረበ መሆኑ፤
 • ለቤተ-መፃህፍቱ የሚያገለግሉ የተለያዩ ሸልፎች በበቂ ሁኔታ ያለ መሆኑ፤
 • በተለይ ትልቁ ቤተ-መፃህፍ ለአንባቢ አመች የሆነ መሆኑ፤
 • የጽህፈት መሳሪያዎች በወቅቱ እየቀረቡ መሆናቸው፤
 • ለብዙ ዓመታት ያልተቆጠሩ የቤተ-መፃህፍት ንብረቶችና መፅሀፎች በ2011 ዓ/ም ቆጠራ መደረጉ
 1. ድክመት (Weakness) የምንላቸው
 • መጽሀፎች መጽሄቶችን እና ጋዜጦች ወደ አዲቪዘዋል ሲሰተም አለመቀየር፤
 • አብዛኛው የቤተ-መፃህፍት ሰራተኞች የኮምፒተር እውቀት ዝቅተኛ መሆን፤
 • አንባቢዎች ተጠቅመው ሲወጡ የፍተሻ አገልሎት ደካማ መሆን
 1. መልካም አጋጣሚ (Opporatanity)
 • የኮሌጁ ሀላፊዎች ለቤተ-መፃህፍቱ ጠንካራን ልዩ ድጋፍ ማድረጋቸው ፤
 • የኮምፒተር አቅርቦት እየተሻሻለ መምጣቱ ፤
 • ከነበረው አስራር በመውጣት ሰራተኞች በአዲስ እንዲደራጁ መደረጉ ፤
 • በሰራተኞች መካከል ተግባብቶ መስራት፤
 • የቤተ-መፃህፍት መስኮቶች በፍርግርግ የተሰራ በመሆኑ ከስርቆት ነፃ መሆኑ፤
 • ለተማሪዎች የኢንተርኔት አገልግሎት ለመስጠት ዕቅድ መያዝ
 • ማየት ለተሳናቸው ተማሪዎች አገልግሎት የሚውል ኮምፒተሮችና ሶፍትዌር እንዲሞላ መደረጉ

 

 1. ስጋት (Threat)
 • ከፍተኛ የሰው ሀይል ችግር ስላለ የአንባቢያን ፍላጎቶች ለማሟላት አለመቻል የስራ ጥራት ያጎድላል፡፡
 • በጀት በወቅቱ ላይለቀቅ ይችላል፤
 • ይገዛሉ ተብሎ በእቅድ የተያዙ መጽሀፎች ከአንባቢያን ቁጥር ጋር ባይመጣጠኑ፤
 • ንብረቱን ለመቆጣጠር ያመች ዘንድ የፍተሻ ሰራተኛ አለመኖር፤
 • ለተማሪዎች የኢንተርኔት አገልግሎት ለመስጠት ዕቅድ ቢያዝም ያለው የተማሪና የሰራተኛ መጠን አለመጣጣም እና ያረጁ ኮምፒተሮች በመሆናቸው አገልግሎት ለመሰጠት መቸገር፤
  • የእቅድ አለማና ግብ
 • የማንኛውም ቤተመጽሀፍትና ዶክመንቴሽ አገልግሎት ዋና አላማ የተቋሙን ት/ትና አላማ ከግብ ለማድረስ ለተማሪዎች ለመ/ራንና ለአስተዳደር ሰራተኞች አስፈላጊውን መፅሀፍት በማሟላት የኮሌጁን በማህራዊና በሶሻል ሚዲያ የዳበረና የበለፀገ ተማሪዎች ከአሁኑ ማግኘት ያለባቸው እውቀት እንዲያገኙ ቤተ-መፃህፍቱ የድርሻውን ይወጣል፡፡
 • በተቋሙ ለሚገኙ መ/ራን የአስተዳደር ሰራተኞች እና ተማሪዎች አስፈላጊውን ድጋፍ በመስጠት በንባብና በጥራትና ምርምር ግላዊ ዕውቀታቸውን በማዳበርና ተማሪዎች ብቁና አገር ተረካቢ ትውልድ ሆነው እንዲወጡ ልዩ እገዛ የሚደረግበት ቦታ ነው፡፡
 • ተማሪዎች ቤተ-መፃህፍት ቢውሉ ከአዲሱ ካሪክለም ጋር በተቀረፁት መፅሀፎች ተጠቅመው ራሳቸው ውጤታማ እንዲያደርጉ እና ሁሉም ተማሪዎች የተሻለ ውጤትና ደረጃ እንዲኖራቸው ማድረግ ነው፡፡
 • ዘመናዊነት የተላበሰ ቤተ-መፃህፍት ማደራጀት፤
 • በቤተ-መፃህፈቱ ዙሪያ ወቅታዊ ችግሮች የመፅሀፍት እጥረት የመሳሰሉትን መፍታት፤
 • ለተጠቃሚዎች ቀልጣፋና ትህትና ባለው መልኩ ማስተናገድ፤
 • የተሻለ አሰራር ካላቸው የቤተ-መፃህፍት የአሰራር ልምድ ልውውጥ ማድረግ፤
 • ያረጁና የተገነጠሉ መጽሀፍትን መጠገን፤
 • የተናጠልና የጋራ ተግባራትን መፈፀም
 • ቤተ-መፃህፍቱ ሊሰጥ ከነበረው 2012ዓ/ም የተሻለ ስራ መስራት ፤
 • የአንባቢያን ፍላጎት ለማጎልበት እና ለማዳበር አስፈላጊውን ክትትልና ድጋፍ ማድረግ፤
 • ወደ ቤተ-መፃህፍት ለሚገቡ አዳዲስ መፅሀፍት የካታሎግና የመለያ ቁጥር ኪስ በማዘጋጀት ለአገልግሎት ዝግጁ ማድረግ፤
 • ቸክሊስት በማዘጋጀት ስራዎችን መቆጣጠር፤
 • የአንባቢያን ብዛትና የመፅሀፍት ክምችት ብዛት እስታስቲካዊ መረጃ መያዝና ለሚመለከተው ማስተላለፍ፤
 • ካርድ ካታሎግ ለሌላቸው መፅፍት ማዘጋጀት፤
 • የተቋሙ ንብረት በአግባቡ መጠቀም
 • አመታዊ ንብረት ቆጠራ እንዲካሄድ ማድረግ፤

የስራ ዘርፉ የ2012ዓ.ም አንኳር ውጤቶች

 • በቤተመጽኃፉ ባለሙያዎች የዕርስ በዕርስ ስልጠና መካhሄዱ
 • ከአጋር ኮሌጆች ጋር የ ልምድ ልውውጥ መደረጉ
 • በፕሮፌሰር ሞገሴ አሸናፊ በስጦታ በርካታ ዘመናዊ ስነ-ሕይወት መሰረታዊያን መጽሃፍት ተበርክተዋል

 

የ2012ዓ.ም ክትትልና ግምገማ ቁልፍ የውጤት  አመልካቾች

ተ.ቁ ተግባራት መለኪያ የ2011ዓ.ም አፈጻጸም የ2012ዓ.ም ዕቅድ የ2012ዓ.ም ዕቅድ በሩብ ዓመት ምርመራ
1ኛ ሩብ ዓመት 2ኛ ሩብ ዓመት 3ኛ ሩብ ዓመት 4ኛ ሩብ ዓመት
1  

ስራ አመራር፣አደረጃጀት፣ውሳኔ አሰጣጥና አተገባበር ሥርአት ተሸሽሏል

1.2 የስራ ዘርፉ እና በስራዘርፉ ስር ያሉ አደረጃጀቶች የ2011ዓ.ም አፈጻጸም ግምገማ/የሁኔታ ትንተና በማድረግ እቅድ አዘጋጅተዋል፣ በእቅድ ተመርተዋል በ%

80%

80%

25%

25%

25%

1.3 ከ2012ዓ.ም ዕቅድን መሰረት በማድረግ ለክትትልና ድጋፍ/ስራን ቆጥሮ ለመስጠትና ለመቀበል የሚያስችል ቼክሊስት ተዘጋጅቷል በ%

80%

90%

30%

35%

20%

1.4 በልዩልዩ የአቅም ግንባታ ሰራተኞች በቁጥር 0 8
1.5 በስራ ዘርፉ ግምገማዊ ውይይት/እቅድ

አፈጻጸም፣ በውጤት ተኮር አፈጻጸም/ የተሳተፉ መምህራን/ሰራተኞች

በቁጥር 8 8 8 8 8
1.6 ሁሉም የሩብ አመት እና በየጊዜው የሚጠየቁ ሪፖርቶች በጥራት ተዘጋጅተው በወቅቱ ተልከዋል   በቁጥር 4 4 1 1 1
1.7 የአገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል ተገልጋችን እርካታ ለማሳደግ የተካሄዱ የሀሳብ መስጫ ሳጥን ማስቀመጥ በቁጥር 1 1 1 1 1
1.8 የላብ ቶፕ ኮምፒተር ስርጭት/ ለመምህራን/ ሰራተኞች/ በቁጥር 0 1 0 0 0
1.10 የኢንተርኔት/ዋይፋይ አገልግሎት/ ለመምህራን/ ሰራተኞች/ በ% 0 99% 0 0 0
1.11 በቤተመጽሀፍት አገልግሎት ያገኙ ተጠቃሚዎች ወንድ በቁጥር 123,213 180,113 30,000 30,350 29,706
ሴት በቁጥር 114,926 140,928 32,800 32,320 20,328

 

የ2012ዓ.ም ክትትልና ግምገማ ቁልፍ የውጤት  አመልካቾች

ተ.ቁ ተግባራት መለኪያ የ2011ዓ.ም አፈጻጸም የ2012ዓ.ም ዕቅድ የ2012ዓ.ም ዕቅድ በሩብ ዓመት ምርመራ
1ኛ ሩብ ዓመት 2ኛ ሩብ ዓመት 3ኛ ሩብ ዓመት 4ኛ ሩብ ዓመት
1..12 የተማሪዎችን ስነምግባር ለማሻሻል በተሰራው ስራ በዲሲፕሊን የተቀጡ ተማሪዎች በቁጥር 16 20 8 10 4
     ግብ
2.1 1.  ለነባርና አዲስ ተማሪዎች፣ ለመምህራንና ሰራተኞች እንዲሁም የቤተ-መፃህፍቱን አገልግሎት ለሚፈልጉ የውጭ ተጠቃሚዎች የንባብና የውሰት አገልግሎት መስጠት በ% 80% 99% 60% 70% 60%
2.2 2.  ወደ ኮሌጁ የሚገቡ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች ስለቤተ-መፃህፍት አጠቃቀም ኦሬንቴሽ በመስጠት በአግባቡ እንዲጠቀሙ ማድረግ፤ በ% 80% 100% 50% 50% 50%
2.3 3.  ሀገራዊና ወቅታዊ መረጃዎችን ተጠቃሚዎች በወቅቱ እንዲያገኙ ለማስቻል የጋዜጦችና መጽሔቶች አገልግሎት መስጠት፤ በ% 90% 100% 70% 75% 80%
2.4 4.  ስለቤተ-መፃህፍት ሙያ፣ አደረጃጀት እና አገልግሎት የስራ ጊዜን በማይነካ መልኩ የግንዛቤ ማሳደጊያ ስልጠና ለስራተኞች መስጠት፤ በ% 80% 80% 60% 70% 50%
2.1.1  መጽሔት፣ ጆርናሎች እንዲሁም ጋዜጦችና መጽሔቶች እንዲገዙ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ማድረግ ግዥው እንዲፈፀም ማድረግ፤ በ% 80% 80% 70% 75% 75%

 

 

 

 

 

የ2012ዓ.ም ክትትልና ግምገማ ቁልፍ የውጤት  አመልካቾች

ተ.ቁ ተግባራት መለኪያ የ2011ዓ.ም አፈጻጸም የ2012ዓ.ም ዕቅድ የ2012ዓ.ም ዕቅድ በሩብ ዓመት ምርመራ
1ኛ ሩብ ዓመት 2ኛ ሩብ ዓመት 3ኛ ሩብ ዓመት 4ኛ ሩብ ዓመት
2.1.2  ጥረዛና ድጎሳ የተደረገላቸው መጽሐፍት በቁጥር 500 600 200 150 200
2.1.3    ወራሃዊ ወደ ቤተ-መፃህፍት የሚገቡ ጋዜጦችንና መፅሄቶች መረከብና መጠረዝ በቁጥር   1053   1053 500 250 400
3  ንዑስ ተግባር
3.1     ለቤተ-መፃህፍት አገልግሎት የሚውል የተለያዩ ቅፆን፣ ካርዳች እና የማዋሻ ፖኬቶችን ማሳተም በ% 60% 60% 0 0 0
3.2     ኮፒያቸው ያነሱና ገፃቸው የተገነጠሉ መጽሀፍትን ፎቶ ኮፒ ማድረግ፤ በ% 60% 70% 50%
3.3    ለቤተ-መጻህፍት አስፈላጊ የሆኑ እስታስቲካዊ መረጃዎችን መያዝ፤ በቁጥር 2 2 2 2 2
3.4    በግዥም ሆነ በእርዳታ የገቡ መጽሐፍትን አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት በማጠናቀቅ ካታሎግና ክላስፊኬሽን ሰጥቶ ለአገልግሎት እንዲበቁ ማድረግ፤ በ% 88% 88% 50% 60% 50%
3.5    በየሩብ ዓመቱ መጨረሻ የቤተ-መፃህፍቱን የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ማቅረብ በ% 90% 90% 60% 65% 70%
3.6     በየሴሚስተሩ የተቀመሩ/ እንዲሰሩ የተደረጉ ተሞክሮዎች/ በቁጥር   3 5 0 0 0
3.7     የመጽሐፍ ግዥ በቁጥር 98 140 0 0 4